ተአምረኛዋ ውድብ
ምንጭ፡ Aiga News
በኢትዮጵያ ያለፉት 31 ዓመታት ውስጥ ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) በኢትዮጵያና በምሥራቅ አፍሪካ የነበራትና ያላት ተጽዕኖ እጅግ ግዙፍ ነው። ነገም ተፅእኖዋ ይቀጥላል። ይህንን ደግሞ እንኳን ወዳጆቿ ጠላቶቿ የሚመሰክሩት ሐቅ ነው።
ከሚታዩትና ፈፅሞ ሊካድ (deny) ሊደረጉ ከማይችሉት ተፅዕኖዎቿ ባሻገር የጠላቶቿ ህልውና ሳይቀር በሷ ላይ የተመሰረቱ ናቸው። ማሳያዎቹም፦
1. የኤርትራው አራዊት ኢሳያስ አፈወርቂና ግብረ አበሮቹ በኤርትራ ውስጥ “ወያኔ”: “የወያኔ ወራር” እያሉ በስልጣን ለመቆየት ተጠቅመውበታል። እውሁንም በመጠቀምም ላይ ይገኛሉ።
1.1 የኢሳያስ interviews for many years: America & ወያኔ – ወያኔ – ወያኔ የሚል ነው። እሷን ሳይጠቅስ interviews የሰጠበት አንዳችም ዕለት የለም። (እሷ ባትኖር ምን የውጠው ነበር?) እንጃ I think ገደል¡።
2. አብዛኛዎቹ የኢትዮጵያ ተቃዋሚ ፓርቲዎች እውቅናንን ያገኙት፣ መግለጫ ቢያወጡ የሚደምቅላቸው፣ የመሪ ተብዮዎቹ interviews እና ንግግር ቢያደርጉ ህ.ወ.ሓ.ት (TPLF) ሳይሉ ፈፅሞ አላለፉም። አያልፉም። (እሷ ባትኖር አብዛኛዎቹ ተቃዋሚዎች ህልውናቸው ምን ይውጠው ነበር?) እግዚአብሔር ይወቀው ማድቤት ውስጥ ሙቅ ሰሪ!።
3. አብዛኛዎቹ የግል ሚዲያዎች፣ websites, activists, bloggers – – – ብዙ ተመልካቾች እና አድማጮች ያገኙትና የሚያገኙት ህ.ወ.ሓ.ት – ህ.ወ.ሓ.ት(ትህነግ) የሚል ነገር ካሰፈሩ ስለመሆኑ የአደባባይ ምስጢር ነው። አለበለዚያ የካቲካላስ ኬት?(የአብዛኞቹ የእንጀራ በር መክፈቻና ማዳበሪያ – የእውቅናቸው መሠረት እሷ ናት። እቺ አልማዝዋ ህወሓት ተሽጣ ተሽጣ የማታልቅ። ከሃዲዎች በዝተው እንጂ ለብዙዎች የዋለችው ውለታ ከወላጅ እናታቸው በላይ የሆዳቸው ቀፈት ሞዪ ናት።)
4. አብዛኛዎቹ You Tubers ብዙ ተመልካቾች የሚያገኙት ህ.ወ.ሓ.ት ነክ ነገር ሲያቀርቡ እንደሆነ እነርሱ አይደለም የአረቂ አቅራቢዋም በደንብ ታውቃለች። የህ.ወ.ሓ.ት አመራሮች ፎቶና መረጃም እጅግ ተፈላጊ ነው። እንደጉድ ይቸበቸባል።(ያለነሱ YouTubes መቼ ይደምቃል?)
5. አብዛኛዎቹ የpolitical issues interviews, documentaries, speakers – – – ወዘተ ህ.ወ.ሓ.ትን ካረገመ መቸ ይደጋገማል? እሷን የሚረግም እጅግ ተፈላጊ የሚዲያዎች ደንበኛ ይሆናል። ከፍ ሲል ደግሞ ያለጊዜው የዳቀነ ዲያቆን። እና እሷን ሳያነሳና ሳይረግም ታዋቂ የሆነ ፓለቲከኛ ተብዮ ማን ነው? እሷን ሳያነሳ የፓለቲካ issues አደረግኩ የሚል ማን ነው? (ያለሷ የኢትዮጵያ ፓለቲካ ጨውና ዘይት የሌለው ምግብ አይደለምን? ያለ ጨውና ያለ ዘይት የሚመገቡት ምግብ እንደምን ያለ ነው?)
6. አብዛኛዎቹ በፓለቲካ ርዕሰ ጉዳይ ላይ የተፅፉና የተቸከቸኩ መጻሕፍት ተብዬዎች እና መጻሕፍቶች በገበያው የደሩትና የሚደሩት ከህ.ወ.ሓ.ት ጋር እንደምንም ሲያያዙ አይደለምን? (እሷን በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ሳያነሳ የተፃፈ የፓለቲካ መፅሐፍ ተብዮ በኢትዮጵያና ከዓለም ከወዴት ይገኛል?) ምናልባት ከአርታንቲካ በስተቀር ካልሆነ።
7. አብዛኛዎቹ የነውረኛው ስርአት ገዥዎች ብዙ ጭብጨባና ሙገሳ ያገኙት እሷን አንስተው አይደለምን?
8. ምንም እዚ ግባ የሚባል ስራ ያልሰሩት ነውረኛነታቸውን ለመሸፈን እሷን ያነሳሉ። ያለሷ ስብሰባቸው አይደምቅም። ትኩረት አያገኝም። እሷን ሳያነሱ የተሰበሰቡት ስብሰባ አለን?
9. ለጥፋቶች ሁሉ እሷን ይጠቅሳሉ። ለጭብጨባና መንጋቸውን ፀጥ ለማሰኘት በሷ ያስፈራራሉ። ያለሷ ጠንካራ በትር ከወዴት ይገኛል? ፕሮፕጋንዳና አጀንዳ ያለሷ መቼ ታስቦ ያውቃል? ሁሉን ነገር ከሷ ጋር በማያያዝ ነውረኞቹ ሴራቸውን ይሸፍናሉ ፣ ነውረኛ ገበናቸውን ይከድናሉ። (እሷ እኮ የነውረኞቹ ፓለቲከኛ ተብዬዎች የአብርሃም በግ ናት። እሷን በመሰዋት በየትኛውም ቦታ ደረታቸውን ነፍተው ያልፋሉ።)
10. ገዥውን የሚያስፈራ ኀይል ቢመጣ በሷ ሰልጥኖ፣ በሷ ተደግፎ፣ ከሷ ጋር ሆነው ይባላል። ለመብቱ የሚታገል በሙሉ ከሷ ጋር ይተሳሰራል። (ከሷ ጋር ማይነሳ የገዥዎች ስጋት የሆነ ኀይል ማን አለ?)
11. ሰውን ለማሰር ቢፈለግ የህ.ወ.ሓ.ት አባልና ደጋፊ ተብሎ ይታሰራል። አባልና ደጋፊ ባይሆን የሷ ሃሳብ ተባባሪ ተብሎ ስሙ ይጠፋል። ሰዎችን ለመጨፍለቅ፣ ለመጨፍጨፍ፣ ለማፈን፣ ለመክሰስ – – – እንደምንም ተብሎ የማይያያዝ ሁሉ ተያይዞ ከሷ ጋር ተጣምሮ ይቀርባል። (ያለሷ ስም እስርና አፈና መቼ ይደምቃል? መቼስ justify ይደረጋል?)
ይህ ሁሉ ታድያ ምንም የማይረባ በወንጀል የታሰረ ሁሉ ከሷ ጋር ተሳስሮ ታዋቂ የሆነበት፣ጅሉ እንደጀግና የተቆጠረበት፣ እንከፍ ፀረ ህዝቡ እንደታጋይ የተቆጠረበት፣ አለፍ ሲልም በሷ መታሰር እንደእድለኛነት የታየበትና የተቆጠረበት ሁኔታ ሳይዘነጋ ማለት ነው። (እሷ እኮ ስንቱን ታዋቂ አድርጋለች? ስንቱንየbiographies ባለቤትና ባለሟል አድርጋለች? ስንቱን በሷ እንዲና እንዲ ሆንኩኝ ብሎ ከሃገር ወጥቶባታል? ስንቱ እኮ በስሟ ሸቅሎባታል?)
ያም ሆነ ይህ ተአምረኛዋ ውድብ እንደመንፈስ በሁሉ ቦታ ስለሁሉ ለሁሉ አለች። መኖሯንም አስመስክራለች።
የውነት ለመናገር ጠላቶቿ የሷን ስም ያነሱትን ያክል ፈጣሪያቸውን ቢያነሱ የውነት ክፍ የሚያወጡ መላዕክት በሆኑ ነበር።
ተአምረኛዋ ውድብ ነበረች – አለች – ትኖራለችም።
ትግራይ ትስዕር!!
ትግራይ ትዕወት!!