ከሳጥናኤል የላቀ ድፍረት ያላቸው የእፉኝት ልጆች
ምንጭ፡ AigaNews
በኢትዮጵያ ውስጥ ነውር ክብር፣ ዝቅጠት እድገት፣ ውርደት ክብረት፣ ድንቁርና እውቀት ተደርጎ መወሰዱን የማያስተውል የለም። ያሁኑ ግን እግዚኦ የሚያስብል፣ ብጹዕ አባታችን እንዳሉት “መፈጠርን የሚያስጠላ” ድፍረት ነው።
በመጽሐፍ ቅዱስ ለይሁዳና ለመሰሎቹ “ባልተወለደ ይሻለው” ተብሎ እንደተጻፈ ከግብራቸው ክፋትና ከሀሳባቸው ቆሻሻነት በተለይም በቤቱ ፣ በቤተ መቅደሱ በፈጣሪ ከሰሩትና በመስራት ላይ ካሉት እልፍ አላፍ ዲያቢሎሳዊ ተግባር የተነሳ ባይወለዱ የሚሻላቸው በመፈጠርና በመወለድ ሰው የሆኑ – በተግባራቸው ከአራዊት፣ የላቁ አረመኔዎች ይባስ ብለው ከሳጥናኤል በላቀ ድፍረታቸው በብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኽሱም ላይ ለከት አልባ ቆሻሻ አንደበታቸው ሲከፍቱ ተመልክተናል።
እንደጋንኤል ክስረት (‘ዳንኤል ክብረት’) የሚሉት የፋሺስቱ ስርአት ፕሮፕጋንዲስት፣ የስርአቱ የሽንት ጨርቅ፣ በግል ስብዕናው እጅግ የረከሰና የተዋረደ:- ባህር ዳር ላይ አንዲት ሴትን ደፍሮ የካደ፣ ሌሎችን ገንዘብ ከፍሎ እያጻፈ የሌሎችን ስራ በስም ያሳተመ፣ ከሌሎች ሰዎች ስራ ላይ እየወሰደ ስምና መቼት በመቀየር እንደራሱ ስራ የሚያቀርብ – በተለያዩ የሥነ ጽሑፍ ዘርፎች የተጻፉን ጽሑፎች ወደ ወግና ተረታ ተረት በመቀየር እንደራሱ ፈጠራ ያቀረበ ሌባ፣ ከተለያዮ ቋንቋዎች ላይ የተገኙ ሃሳቦችን ወደ አማርኛ በመቀየርና በወግ መልክ በማቅረብ ሌብነትን እንደስራ የሌሎችን ስራ በሙሉና በከፊል ለነሱ ተገቢ እውቅና ባለመስጠት የሚገለብጥ መሰሪ ቆርቆሮ፣ ከ50 ዓመት በላይ ሆኖት ከመንደር ወሬዎች እና ከተረታ ተረት ፍተላዎች ያልወጣ እንከፍ፣ በሴራና በማስመሰል የተካነ በሁሉ ጉዳይ ላይ አዋቂ ነኝ ብሎ ያለ እውቀት በድፍረት – ያለ ጥበብ በማስመሰል – ያለ ማስተዋል በኔትወርክ እና በሴራ የተካነ የሰው እንከፍ በብጹዕ አባታችን እውነተኛ፣ ሐቀኛና ወቅቱን የጠበቀ አባታዊ መግለጫ ላይ ‘መልስ’ ለመስጠት ሞክሯል።
እንደው ለመሆኑ ሰው እግዚአብሔርን ባይፈራ አንድን ታላቅ የብዙ ሚሊዮኖች የመጨረሻ የቤተክርስቲያኗ ፓትርያርክ የሆኑ አባት የተናገሩትን ለማስተባበል አንድ ተራ ግለሰብ እንደምን ይደፍራል? አለም ያወቀውን እውነት – ቢሊዮኖች የሰሙትን እውነት – በማስረጃ የታየን – እንደው ሰው ምን ይለኛል አይባልም? እንዲህ ያለ ድፍረትስ ራስንና ሌሎችን ከመናቅ ድንቁርና ውጪ ምን ሊሆን ይችላል?
የዘር ማጥፋት፣የጦር ወንጀልና የወረራው ዋነኛ ባለቤት የሆነው ፋሺስት ስርአት ገረድ የሆነ ሰው ስለፍጻሜው ምላሽ ለመስጠት ምን ሞራላዊ ብቃት አለው? ገዳይና አቃጣይ – የግድያውና የማቃጠሉ ደጋፊ እንደምን ራሱን ለመከላከል ይመጣል? አንድ ተራ በምግባሩ በአደባባይ የረከሰና የተጨማለቀ ሰው ብጹዕ ወቅዱስ የሆኑ ፓትርያርክ ለመናገር እንዴት ይችላል? ሰው ደረጃውን ሳያውቅ ተራ የስም ማጥፋት ስራ ይሰራ ዘንድ የፈቀደለት ማን ነው?
ብጹዕ ወቅዱስ አባታችን ታፈንኩ ሲሉ ማን ደረሰላቸዉ? ከአፋኞች ወገን ሆነው ያፈኗቸው ሰዎች ዛሬ በሳቸው ላይ አንደበታቸው ይከፍቱ ዘንድ ማን ድፍረቱን ሰጣቸው? ፓትርያርኩ ታፍነውበት ዝም ያለ ምዕመን እንደምን ያለ አዚም የተደረገበት ምዕመን ነው? ፓትርያርኩ ታፍነውበት መታፈናቸው ሳይሰማው ከአፋኞች ወገን ሆኖ የሚያሸረግድ መንፈሳዊ ማህበራት፣ቤተ ክህነት (በተግባር ቤተ ክህደት የሆነ)፣ጳጳስነት፣ ዲያቆንነት ከወዴት ያለ ነው? አጠገሙ የሚያያቸውና የሚሰማቸውን ፓትርያርክ የማያከብርና ያላከበረ ክርስትና – ያላየውና ያልሰማውን ፈጣሪ አከብራለው የሚል ማነው? ዕውን የሳቸውን እንባ ፈጣሪ አይመለከትም? ዕውን የሳቸውን መታፈን – ሐዘን – ጭንቀት – ያሉበትን ሁኔታ ፈጣሪ አያውቅምን? አይፈርድምስ? የሳቸውን ድምጽ ለማፈንና ላለማሰማት የተጉ አንደበቶች ዋጋቸውን ያገኙ ዘንድ አይቻልምን?
ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ለቤተ ክርስቲያን የከፈሉት መስዋዕትነት እጅግ ትልቅ ነው። ለአመታት በውጭ ሃገራት ተሰደው የኖሩት በቤተ ክርስቲያን ላይ የተሰራን ሸፍጥ በጽኑ በመቃወማቸው ነው። ላመኑበት በተግባር ዋጋ የከፈሉ፣ ለማንም የማያጎበድዱ ታላቅ አባት መሆናቸውን ታሪካቸው አቢይ ማሳያ ነው። ስለቤተ ክርስቲያን ሥርአትና ህልውና ሽንጣቸውን ገትረው ተከራክረዋል። ጽፈዋል፣ዋጋ ከፍለዋል።
በትግራይ ሕዝብ ላይ የደረሰውና በመድረስ ላይ ያለው በደል፣ በሰው ልጆች የሚፈፀመው ግፍ እና ጭካኔ የተሞላበት ጭፍጨፋ እኮ ቅዱስ አባታችን እንዳሉት ቁጥር ስፍር የለውም፣ ተገልፆ የሚያልቅም አይደለም። እንደክርስትና አስተምህሮት ክርስቶስ “ፍጹም አምላክ – ፍጹም ሰው” እንደሆነው ሁሉ “አምላክ ሰው – ሰው አምላክ የሆነበት” እንደሆነ ይታወቃል። ሰው ተፈጥሮው ቤተ መቅደስ፣ ሰው ራሱ ቤተ ክርስቲያን ነው። የተጋሩ ከነህይወቱ መቃጠል ለገባው እና ላስተዋለ የተቃጠለው ክርስቶስ፣ የተቃጠለው ቤተ መቅደስ፣ የተቃጠለው ቤተ ክርስቲያን ነው። ለገባው እና ላስተዋለ ፈጣሪ በአምሳሉ የፈጠረው ፍጥረት መቃጠል – መጨፍጨፍ እና መገደል ጥሉ ከተሰሪው ሳይሆን ከሰሪው ጋር ነው። ሰሪውም ፈጣሪ ነው። ከፈጣሪ ጋር ገጥሞ ፈጣሪን ያሸነፈ ከቶ የለም። አይኖርምም።(ቅዱስ አባታችን በጥኡም ልሳናቸው ገልጸውታል።)
ፈጣሪን የያዘውን – ፈጣሪ የመረጠውን – ፈጣሪ ለመምረጡም በታቦተ ጺዮን መገኛነት፣ በ9ኙ ቅዱሳን ማረፊያነት፣ በቅዱሳን ቦታዎቿና በተግባር የትግራይ ሕዝብ survive ማድረጉ ትልቅ ማሳያ ነው። ከፈጣሪ ጋር የሆነውን የትግራይ ሕዝብ ከቶ ማሸነፍ – ማጥፋትም አልተቻለም። ፈጽሞም አይቻልም።